ናፈቀኝ! … እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)

ETHIOPIA | “ናፈቀኝ… ደገኛው ቄስ ሞገስ፥ በፈረስ፣ በበቅሎ ተጉዞ ሲመጣ፥
ለዓመት በዓል ጨዋታ፥ ሰው እልል እያለ ሲቀበል በእምቢልታ፤

አንተዬ… በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ፤ ያገሩ ገነኛ ሆ እያለ ሲመጣ፣
አባዬ ናፈቀኝ የከብቶቹ ጌታ፥ ሲባርክ ሲመርቅ የቤቱን ጨዋታ፤

እምዬ እናታለም….
ጉልበትሽ ችሎታሽ ይበልጣል ከሺህ ሰው፥
__ ይኸው ሰውን ሁሉ እጅሽ አጠገበው፤

ናፈቀኝ… ያያ ታዴ ሆዴ…
“የሽመል አጓራ አይችልም ገላዬ
የኔ ሆድ አሌዋ ና ቁም ከኋላዬ፤
አያና ድማሙ አያና ድማሙ
አያና ድማሙ አያና ድማሙ፤

ዓባይ ወዲያ ማዶ ትንሽ ግራር በቅላ
ልቤን ወሰደችው ከነሥሩ ነቅላ።”
እያለ ሲዘፍን ትዝታው ገደለኝ
ዛሬ በሰው ሀገር የሰው ከብት እያየሁ እያንገበገበኝ

ወኻ ጃሪ ወኻ ኮሎ ሲሉ
ያባቴን በሬዎች የእናቴን መሰሉኝ፤”

~ እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)

Source Article from http://getutemesgen24.com/%E1%8A%93%E1%8D%88%E1%89%80%E1%8A%9D-%E1%8A%A5%E1%8C%85%E1%8C%8B%E1%8B%A8%E1%88%81-%E1%88%BD%E1%89%A3%E1%89%A3%E1%8B%8D-%E1%8C%82%E1%8C%82