የላይቤሪያ ቀጣዩ ፕሬዘዳንት ጆርጅ ዊሃ ስልጣኑን ተረከበ

አባይ ሚዲያ ዜና

የላይቤሪያ ቀጣዩ ፕሬዝዳንት የቀድሞው የእግር ኳስ ኮከብ ጆርጅ ዊሃ የፕሬዝዳትነት መንበርን ተረከቡ:: በላይቤሪያ ዋና ከተማ ሞኖሮቪያ በሚገኘው ስታዲየም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በታደሙበት የሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዋና ዳኛ ፊት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል::

በዚሁ የቃለ መሃላ ስነ ስርዓት ላይ ታዋቂው የእግር ኳስ ተጫዋች ሳሙኤል ኤቶ ጨምሮ ከጆርጅ ዊሃ ጋር አብረዋቸው ኳስ የተጫወቱ እንዲሁም የጋና: የሴራሊዮን እና የጋቦን ፕሬዝዳንቶች ተገኝተዋል::

የሃገሪቱ ዜጎች የላይቤሪያን ባንዲራ እያውለበለቡ በመደነስና በመጨፈር በበአለ ሲመቱ ላይ ለመታደም ስታዲየሙ በር ላይ ተሰባስበው ሲጠባበቁ ነበር::

ላይቤሪያን ለ 12 ዓመታት የመሩት ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሌፍ ለአዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ለ 51 ዓመቱ ጆርጅ ዊሃ ስልጣኑን በይፋ አስረክበዋል:: ፕሬዝዳንት ዊሃ ስልጣኑን ከተረከቡ በኋላ ኤለን ጆንሰን የኖቤል የሰላም ሽልማት የተሸለሙና አሁን በሃገሪቱ ለሚታየው ሰላም መሰረቱን የጣሉ ታላቅ መሪ ነበሩ በማለት ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ በቀጣይ በሃገሪቱ ቅድሚያ በመስጠት ሊያከናውኑ ያቀዱትን በንንግር ለህዝባቸው ይፋ አድርገዋል    

Source Article from http://amharic.abbaymedia.info/archives/41617