አርበኞች ግንቦት 7 በተለያዩ ከተሞች ቀስቃሽ ጽሁፎችን ማሰራጨቱ ተነገረ

የጥምቀትን በዓል ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ከተሞች የተሰበሰበው ህዝብ ህወሃት በአገራችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍና ሰቆቃ አደባባይ ወጥቶ እንዲያወግዝና የተጀመረውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል እንዲቀላቀል ጥሪ የሚያስተላለፍ ብዛት ያላቸውን በራሪ ጽሁፎች አዘጋጅቶ እንዳሰራጨ የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ቀጠና ለትንሳኤ ሬዲዮ በላከው መረጃ ገለጸ።

ንቅናቄው በራሪ ጹሁፎች ካሰራጨባቸው ከተሞች ውስጥ  አዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳርና ወረታ ይገኙበታል። በጎንደር፣  በባህር ዳርና በወረታ በተሰራጩት የቅሰቅሳ ወረቀቶች የብአዴን አባላትና ካድሬዎች ህዝባችን ለነጻነቱ የሚያካሂደውን ትግል እንዲያግዙ ጥሪ ያዘለ  መልዕክት ጭምርም መሆኑ ተነግሯል።  ንቅናቄው የበተነውን ወረቀት ህዝብ እየተቀባበለ ማንበቡና በርካቶችም በራሪ ጽሁፎቹን እያባዙ በስፋት እንዲዘዋወር እያደረጉት እንደሆነ የገለጸው የንቅናቄው፣ መረጃ አባላቱ ከምንጊዜውም በላይ ድፍረት በተሞላበት እርምጃ ጽሁፉን አንብበው መረዳት ለማይችሉ ሁሉ  እያነበቡ ሲገልጹ ውለዋል ብሏል።

ይህ በዚህ እንዳለ፣  ጥር 11 ቀን 2010  ነዳጅ ከሱዳን ጭኖ ወደ አገር ቤት በመምጣት ላይ የነበረ አንድ ቦቴ  መኪና ጭልጋ ከተማን እንዳለፈ ጓንግ ወንዝ አጠገብ  ከቀኑ 11 ሰዓት ተኩል ላይ ተመትቶ እንደተገለበጠና በውስጡ የነበረ አጃቢ እስከነሾፌሩ ህይወታቸው እንዳለፈ ለማወቅ ተችሏል። ነዳጅ በጫነው በዚህ ቦቴ መኪና ላይ እርምጃ የወሰዱት የነጻነት ታጋዮች ንብረትነቱ የህወሃት መሆኑን ካረጋገጡ ቦኋላ መሆኑን ገልጸዋል።

Source Article from http://amharic.abbaymedia.info/archives/41612