የኬኒያ ፍርድ ቤት የኬኒያታን ምርጫ አጸደቀNovember 20,2017,14:00

****በወንድወሰን ተክሉ****

በተቃዋሚዎች፣በአክቲቪስቶችና በገዢው ፓርቲ ሲጠበቅ የነበረው የኬኒያ ጠ/ይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ዛሬ የፕሬዚዳንት ሁሩ ኬኒያታን ሁለተኛ ዙር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ህጋዊነትን በማጽደቅ ዛሬ ውሳኔ ሰጠ።

በጥቅምት 26ቀን 2017በተካሄደው የኬኒያ ሁለተኛ ዙር ምርጫ ላይ ተቃዋሚው ያቀረብካቸው ቅድመ ሁኔታዎች አልተማሉልኝም በማለት እራሱን ከምርጫው ያገለለ ሲሆን የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ብቻ በተሳተፉበት ምርጫ ፕሬዚዳንት ሁሩ ኬኒያታ በ98%ድምጽ አሸናፊ ተብለው በሀገሪቱ ምርጫ ቦርድ ኮሚሽን መታወጁ ይታወሳል።

የኬኒያ ሀገር አቀፍ ምርጫ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ በነሀሴ 8ቀን 2017 ተካሄዶ የነበረና ፕሬዚዳንቱን አሸናፊ አድርጎ አውጆ የነበረ ቢሆንም በተቃዋሚው በኩል በተከፈተ ክስ ጠ/ይ ፍርድ ቤቱ ምርጫው ተጭበርብራል በሚል ውሳኔ ሁለተኛ ዙር ምርጫ እንዲካሄድ መወሰኑ ይታወቃል።

በሁለተኛው ዙር ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ተቃዋሚው ናሳ [National Super Alliance (NASA)]ገዢው የኢዮቤልዩ ፓርቲ [Jubilee ] እና የሀገሪቱ ምርጫ ቦርድ [IEBC]ማስተካከል የሚገባቸውን ያላቸውን ባለ 11ነጥብ ቅድመ ሁኔታን ቢያቀርብም በገዢው ፓርቲ በኩል ተቀባይነትን እንዳላገኘ ይታወቃል።

በዚህም ምክንያት ኬኒያ በእስከዛሬው አሸናፊ ፕሬዚዳንት ያልታወጀባት ሀገር ስትሆን የጠ/ይ ፍርድ ቤቱ የዛሬው ውሳኔ ይህንን ክፍተት እንደሚሞላ የተጠበቀ ሲሆን በተቃዋሚው በኩል ብሔራዊ ንቅናቄ በሚል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ዓመጾችን በማካሄድ መብቴን አስከብራለሁ የሚል ውሳኔን በማስተላለፉ የሀገሪታን ሁኔታ ያልተረጋጋች አድርጋታል ሲሉ ዲፕሎማቶች ይናገራሉ።

Source Article from http://www.mehaderezena.com/amharic/%E1%8B%A8%E1%8A%AC%E1%8A%92%E1%8B%AB-%E1%8D%8D%E1%88%AD%E1%8B%B5-%E1%89%A4%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%8A%AC%E1%8A%92%E1%8B%AB%E1%89%B3%E1%8A%95-%E1%88%9D%E1%88%AD%E1%8C%AB-%E1%8A%A0%E1%8C%B8%E1%8B%B0/