በባህርዳር ከተማ ቦንብ ፈንድቶ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ

አባይ ሚዲያ ዜና
በጸሎት አለማየው

ዛሬ ዕለተ ቅዳሜ ነሐሴ 6 ቀን 2009ዓ/ም ከምሽቱ 3:05 ሲሆን በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 04 ብሔራዊ ሎተሪ አካባቢ በሚገኘው ካሪቡ ካፌ ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈፀመ፡፡

 የካሪቡ ካፌ ባለቤት የመንግስትና የስርአቱ ዋና ድጋፍ ሰጪ እንደሆኑ በስፋት በሚነገርበት ወቅት ይህ የቦምብ ጥቃት በንግድ ድርጅታቸው ላይ መፈጸሙ ሆን ብሎ ሳይሆን እንዳልቀረ እየተነገረ ይገኛል።

 በከተማው በተደረገው የአድማ ጌዜም ከህዝቡ ጎን በመቆም መንግስት በክልሉ የሚፈጽመውን የመብት ጥሰትና ጭቆና ከመቃወም ይልቅ ስርአቱ በመደገፍ እንደቆዩም ከቦታው የደረሰን ሪፓርቶች ያመለክታሉ።

 ፍንዳታው በተከሰተበት በዚህ ድርጅት አካባቢ ከፍተኛ መተራመስ እንደተፈጠረና ሁለት ሰዎች እንደተጎዱ ከደረሰን መረጃ መረዳት ችለናል፡፡

 መንግስት ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ኃይል በማሰማራት መንገዶቹንም ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ተጨማሪ መረጃ ወደ ሚዲያ እንዳይወጣ እየተከላከለም እንደሆነ ሪፓርቶሮቻችን ገልጸውልናል።

በጠቅላላው በዚህ የቦምብ ጥቃት የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት የምናደርገውን ሙከራ እየቀጠልና ዝርዝር መረጃዎች ሲደርሰን የምናሳውቅ መሆኑንም እንገልፃለን።

 

Source Article from http://amharic.abbaymedia.com/archives/34095