ከኬንያ ምርጫ በኋላ ኡሁሩ ኬንያታ አሸነፉ ሲባል አመጽ ተነስቶ ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

አሶሲዬት ፕሬስን ጠቅሶ ዎል ስትሪት ጆርናል የተሰኘው ጋዜጣ ከኬንያ ምርጫ በኋላ ኡሁሩ ኬንያታ አሸነፉ ሲባል አመጽ ተነስቶ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል።

ግድያው የተፈጸመው የኡሁሩ ተቀናቃኝ የሆኑት ራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች ብዛት አላቸው ከሚባልበት ኪሱሙ ከተሰኘው ከተማ ነው። በተጨማሪ አምስት ሰዎች እንደቆሰሉም ተነግሯል።

ቅዳሜ የኬንያ ፖሊስ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች ላይ ጥይት ሲተኩሱ የአሶሲዬት ፕረስ ጋዜጠኖች ፎቶ አንስተዋል። ማታሬና ኪቤራ ከተሞች ላይም ተመሳሳይ ግⶽት ተከስቷል ብሏል።

በአብዛኛው የኬንያ 45 ሚሊዮን ህዝብ ጸጥ እንዳለ ነው ይላል ዎል ስትሪት የምርጫው ውጤት ከተነገረ በኋላ። ኡሁሩ ኬንያታ “በወዳጅነት እጄን እዘረጋለሁ” ይላሉ ለተቃዋሚው ወገን። ቢሆንም ምርጫው ተሰርቋል። የምርጫ ቡርዱ የኮምፑተር መዝገብ በሰርስሮ ገቦች ተደፍሮ ምርጫው ተሰርቋል በማለት ራይላ  ኦዲንጋ እና ደጋፊዎቻቸው አሁንም ይናገራሉ።

የኬንያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለሰላም እየተማጠነች ነው። “በምርጫ ምክንያት ሰው መሞት የለበትም” ትላለች። ሁኔታው ግን አልተረጋጋም።

በተመሳሳይ ሪፖርት ደግሞ ሬውተርስ አስራ አንድ ሰዎች መሞታቸውን ዘግቧል።

Source Article from http://amharic.abbaymedia.com/archives/34076