የደቡብ ኮሪያ መንግስት ለሰብዓዊ ዕርዳታ የሚውል 1 ሚሊዮን ዶላር ለገሰ

አባይ ሚዲያ ዜና

ናትናኤል ኃይለማያም

የደቡብ ኮሪያ መንግስት አዲስ አበባ ባለዉ ኢምባሲዉ አማካኝነት በሰጠዉ መግለጫ ለሰብዓዊነት ጉዳይ የሚዉል የእርዳታ ገንዘብ መስጠቱን አስታወቀ።

ከዚሁ የአንድ ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ እርዳታ 400 ሺ ዶላሩ ከሰብዓዊነት ጋር ለተያያዘ የሚዉል ሲሆን 500 ሺ ዶላሩ ከዩኒሴፍ ጋር ለተያያዘ እርዳታ የሚዉል መሆኑንም አስታዉቋል።

የተቀረዉ 100 ሺ ዶላር ከአረብ አገራት ወደ አገራቸዉ ያለፈቃዳቸዉ በግዳጅ እንዲመለሱ ለተገደዱት ኢትዮጵያዉያኖች መቋቋሚያ የሚዉል እንደሆነ አዲስ አበባ ከሚገኘዉ የኮሪያ ኢምባሲ የወጣዉ ሪፖርት ያሳያል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ተብሎ ከሕዝብም ሆነ ከተለያዩ ድርጅቶች የሚያገኘዉን የገንዘብ ዕርዳታ አብዛኛዉን ጊዜ የሚያዉለዉ የባለስልጣኑን የግል ፍላጎት ማርኪያ እና የስርዓቱን የአገዛዝ እድሜ ለማራዘሚያ ለሚያስፈልጉ ግብዓቶች እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ቅሬታቸው ያስታውቃሉ።

በቅርቡ በቆሼ በመባል በሚታወቀዉ ስፍራ በኢትዮጵያዉያኖች ላይ በደረሰዉ የሰዉ ሠራሽ አደጋ ከግለሰቦችና ከዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ችግሩ ለደረሰባቸዉ ሰዎች እንዲዉል የተሰጠዉን የገንዘብ ዕርዳታ አገዛዙ ለስልጣን ማራዘሚያ እንዲዉል ማድረጉ ብዙዎች እንደ ምሳሌ የሚጠቅሱት ነዉ።

አሁንም በተለይ ከሳዉዲ አረብያ የሚመለሱት ኢትዮጵያዉያኖች ይህን ገንዘብ ይደርሳቸዋል ተብሎ የማይታሰብ እንደሆነ ብዙዎች ስጋታቸዉን እየገለጹ ይገኛሉ።

አገዛዙም አሁን ባለበት ከፍተኛ የገንዘብ እጦት ምክንያት በምንም መልኩ በግዳጅ ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ ለተገደዱት ይዉላል ተብሎ እንደማይታሰብ ከታዛቢዎች ያገኘነዉ አስተያየት ያስረዳል።

 

Source Article from http://amharic.abbaymedia.com/archives/34071