አገዛዙ በወልቃይት ብጥብጥ ፈጥሮ ወጣቶችን ለመግደልና ለማሰር ተዘጋጅቷል

አገዛዙ በወልቃይት ብጥብጥ ፈጥሮ ወጣቶችን ለመግደልና ለማሰር ተዘጋጅቷል፤ (Muluken Tesfaw)

የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄን ከመመለስ ይልቅ የተለያዩ ሴራዎችን የሚፈጥረው ሕወሓት አሁን ደግሞ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ ዐማራዎችን ለማጥፋት አዲስ ሴራ መጠንሰሱን ነው ምንጮች የጠቆሙት፡፡

ይኼውም በወልቃይት አዲረመጽ ከተማ መግቢያና መውጫ ላይ ኬላዎችን በመሥራት በክልሉ ልዩ ኃይል ፖሊሶች ያስከበበ ሲሆን ሆን ብለው ብጥብጥ ለመፍጠርም እየጣሩ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ሕወሓት የትግራይ ሠፋሪዎችን አስቀድመው ዝግጁ እንዲሆኑም ውስጥ ለውስጥ መልዕክት የተላለፈ ሲሆን በሚፈጠረው ጠበ ተሰሚነት ያላቸውን ሰዎች በመግደልና በማሰር የታሰበ ነው፡፡ የአዲ ረመጥ ወጣቶችም ሕዝቡ በንቃት ጉዳዩን እንዲጠባበቅ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በአዲ ረመጥ ከምንጊዜውም በተለይ ሁኔታ ውጥረት መንገሱንም ገልጸውልናል መረጃዎቻችን፡፡