ከዩ ኤስ አሜሪካ ወደ ካናዳ የሚፈልሱ ስደተኞች ቁጥራቸው በዝቷል

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

የዩ ኤስ አሜሪካ እና ካናዳ ድንበር የሆነው የሮክስሃም መንገገድ ከአሜሪካ ወደ ካናዳ መሸጋገሪያነት ለምን ተወደደ የሚል ጥያቄ አሁን አሁን እየተበራከተ መምጣቱን በተለያዩ ሶሻል ሚዲያ ከሚሰራጩት ዘገባዎች መረዳት ተችሏል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥገኝነት ፈላጊዎች ከአሜሪካው ኒው ዮርክ ግዛት ወደ ካናዳ እየፈለሱ በሚገኙበት በዚህ ወቅት የካናዳ መንግሥት ወታደሮቹን በድንበሩ በማሰማራት ለጥገኝነት ጠያቂዎች መቆያ የሚሆኑ ድንኳኖች እንዲተከሉ ማዘዙ ተዘግቧል።

“25 ትላልቅ ድንኳኖች፣ መብራትና ሙቀት በተጨማሪ የሳንቃ ወለል ያሏቸው ድንኳኖችን በማዘጋጀት ወደ 500 ጥገኝነት ፈላጊዎችን ለማስተናገድ መዘጋጀቱንም የካናዳ መንግሥት አሳውቋል።

የስደተኞች ህልም የሆነችው የጠቅላይ ሚኒስትር ጁስቲን ትሩዶ ካናዳ በህጋዊ መንገድ ብቻ ሳይሆን ድንበር በመጣስ ለሚመጡ ስደተኞች ለየት ያለ ህግ ማዘጋጀቷ ከሌሎች አገራት ለየት እንደሚያደርጋትም እየተነገረላት ይገኛል።

የካናዳ ህግ አውጭዎች በተቃራኒው እንዲህ ድንበርን ለስደተኞች መክፈት ህገወጥ ፍልሰትን ለመቀነስ ማስተማመኛ መፍትሄ አይሰጥም በማለት ነቀፌታቸውን ሲሰነዝሩ ይደመጣል።

“ነጻ መግቢያ ትኬት አይደለም፤ በፍጹም፤ ሰዎች ሶሻል ሚዲያ ላይ እንደሚያወሩት ወዲያው ጥገኝነት የሚያስገኝ አይደለም” በማለት ይህን የካናዳ መንግሥት በስደተኛ በኩል ያለውን አካሄድ እየተቹ ይገኛሉ።

ብዙ ስደተኞች ከአሜሪካ ወደ ካናዳ በጸረ ስደተኛ ንግግር አድራጊው ዶናል ትራምፕ ፖሊሲ ምክንያት ይጎርፋሉ ተብሎም ይጠበቃል።

Source Article from http://amharic.abbaymedia.com/archives/34009