ባህር ዳር በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስር ናት ተባለ

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

በባህር ዳር የተሰማራው ሰራዊት ከተማይቱ ዛሬም ጭምር በአስቸካይ ግዜ አዋጅ ስር እንዳለች የሚመሰክር ድርጊት ሆኖ ታይቷል።

በከተማዋ የፈሰሱት የስርዓቱ ታጣቂዎች መንደሮችዋን በማጥለቅለቅ የወታደራዊ እዝ መነሃሪያ ያስመሰላት ሲሆን ባለሃብቶችንም እያደኑ የማሰር ተግባር በማጧጧፍ በቀበሌ 1 ያለው ፖሊስ ጣቢያ በእስረኞች ለመጨናነቅ እንደበቃ ኢሳት የአካባቢውን ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል።

በፍልስታ ጾም ምክንያት የእስር አፈሳው ሰለባ የሆኑትን ባለ ሉካንዳ ቤቶች ጭምር መታሰራቸውን ማወቅ የተቻለ ሲሆን ሰኞ እለት ታስቦ በዋለው የሰማእታቱን ቀን በመዘከር የንግድ ተቋሞቻቸውን ለአገልግሎት ክፍት ያላደረጉትን ባለሀብቶች የማሰሩ እርምጃ እንደቀጠለ ለማወቅ ተችሏል።

በአንጻሩም በእለቱ አግልግሎት በሰጡት የስርዓቱ ደጋፊዎች ላይ የቦምብ ጥቃት ይፈጸሟል በሚል ከተማዋን በአሳሽና ፈታሽ ሰራዊት ማጥለቅለቁን የስርዓቱን ከህዝብ ጋር የተጋባውን የጠላትነት ደረጃ በጉልህ ያሳያል ሲሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ከሰኞው የነሀሴ 1 ቀን 2017 የሰማእታቱን ዘካሪ የስራ ማቆም አድማ ግዜ ጀምሮ ከተማዋ በታጣቂ ሰራዊት መጥለቅለቋና ህዝቡም እየተዋከበ፣ እያታፈሰና ብሎም በየስፍራውና በየቤቱም እየተፈተሸ መሆን የተነሳ የተባለው ያአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በባህር ዳር ላይ እንዳልሰራና ከተማይቱም ዛሬም ጭምር ተነሳ በተባለው አዋጅ ስር እንዳለች ተግባራቸው ምስክር ነው ሲሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

Source Article from http://amharic.abbaymedia.com/archives/34023