ምርጫ ቦርድ አሸናፊውን ነገ አሳውቃለሁ ሲል፣ ተቃዋሚው፣ አሸንፌአለሁ ብሏል። በጋሪሳ ዓመጽ ብዙ ንብረት ወደመ

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

በሰላም የተጠናቀቀው የኬኒያ ምርጫ ወደ ደም አፋሳሽ ዓመጽ ቀስቃሽነት ሊቀየር ይችላል የሚለው ስጋት ከመቼውም ግዜ በላይ ዛሬ ጎልቶ ታይቷል። በጋሪሳ ከተማ በተነሳ ዓመጻ የንግድ ማእከሉ የእስራት ሰለባ ሲሆን በናይሮቢ ኪቢራ፣ ማዳሬ ያቆጠቆጠው የዓመጽ ሃይል በገሀድ መታየት ጀምሯል።

የኬኒያ ምርጫ ቦርድ በሁለቱ ብርቱ ተፎካካሪዎች መካከል አሸናፊውን ነገ አስታውቃለሁ ባለበት ቅስፈት የተቃዋሚው መሪ አቶ ራይላ ኦዲንጋ የመራጮች ውጤት ያሉትን ቁጥር በመግለጽ የምርጫው አሸናፊ መሆናቸውን በመግለጽ እስከአሁን በምርጫ ቦርዱ ከተገለጸው የመራጮች ቆጠራ የተለየ ውጤት አቅርበዋል።

በ3፡00 ሰዓቱ [9፡00ፒ ኤም] ዜና እወጃ ላይ አቶ ራይላ ኦዲንጋ የምርጫው አሸናፊ የሚያደርጋቸውን የመራጮች ድምጽ ይዘው የቀረቡ ሲሆን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታን በሚሊዮን ቁጥር ብልጫ እንደሚበልጡ ያሳያል። ሆኖም የአቶ ራይላን የመራጮች ድምጽ ውጤት በምርጫ ቦርድ ያልተደገፈ ሲሆን እስከ አሁን ባለው ውጤት መሰረት እንደ የምርጫ ቦርዱ ገለጻ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ በመሪነት ድምጽ እንዳገኙ ይገልጻል። ሆኖም ይህንን ውጤት ነው ተቃዋሚው እንደተጭበረበረ በመግለጽ እንደማይቀበል ያሳወቀው።

በቀድሞው የደደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ታቦ እምቤኪ የሚመራው የአፍሪካ ሕብረት ታዛቢ ቡድን እና በጆን ኬሪ የሚመራው የካርተር ማእከል ታዛቢ ቡድኖች ተቀራራቢ የሚባል መግለጫ የሰጡ ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች በምርጫው የታዘባቸው ህጸጾች መከሰታቸውን ጠቅሰው ህኖም ህጸጾቹ አጠቃላይ የምርጫውን ሂደትና ውጤት ይለውጣሉ ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል።

ከናይሮቢ 400 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ባለችው የጋሪሳ ከተማ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በተነሳ ብጥብጥ የከተማው የንግድ ተቋማት በእሳት እንደተቃጠሉ ፖሊስ የገለጸ ሲሆን ማምሻው ላይ ዓመጹና እሳቱን መቆጣጠር መቻሉንም አክሎ ገልጿል።

image

 

በጋሪሳ ከተማ በሀሰን ዱዋሌ እና ሀሰን ፋራ ማሊም በሚባሉ ፖለቲከኞች ደጋፊ በተነሳ ብጥብጥ በርካታ የንግድ ቤቶችና ነዳጅ ማደያ በእሳት እንደጋየ ፖሊስ የገለጸ ሲሆን በህይወት ላይ እስከአሁን የአንድ ሰው ሕይወት በተተኮሰ ጥይት መጥፋቱን ሲገልጽ ዓመጹንም መቆጣጠሩን ፖሊስ አስታውቋል።

ዛሬ ማምሻውን የተቃዋሚውን መሪ የአሸንፌአለሁ መግለጫ እና በአንጻሩም የምርጫ ቦርድን ነገ አስታውቃለሁ ውሳኔን ተከትሎ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን ማስተዋል የተቻለ ሲሆን በናይሮቢ እንደነ ኪቢራ፣ መዳሬ፣ ካሪዮባንጊ ሰፈሮች ከወዲሁ ለዓመጽ የተዛጋጁ የተቃዋሚው ደጋፊዎች እንቅስቃሴ ጋር ፖሊስ ግብግብ ላይ እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቃዋሚው ጠንካራ ይዞታ ተብለው በሚታወቁት የሞምባሳና ኪሱሙ ከተሞች ለዓመጽ ባኮበኮቡ ወጣቶችና ፖሊሶች መካከል ተፋጠው እንደቆሙ የታየ ሲሆኑ ወጣቶቹም እየተጠባበቁ ያሉት የመሪያቸውን አቶ ራይላ ኦዲንጋን ያሸነፍነውን ምርጫ ተሰርቀናል የሚለውን መግለጫና የምርጫ ቦርድ የፕሬዚዳንቱን አሸናፊነት የሚገልጸው ጠቅላይ መግለጫ እንደሆነ ይታወቃል።

ተቃዋሚው ራይላ ኦዲንጋ ዛሬ ማምሻውን እንደገለጸው ነገ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫው አሸናፊን ሌላው እጩ ማለትም ፕሬዚዳንቱ ነው ብሎ ከገለጸ ኬኒያ ወደ አስከፊ የእርሰ በርስ ብጥብጥ ውስጥ እንደምትገባ ከወዲሁ እየተነገረ ነው ያለው።

Source Article from http://amharic.abbaymedia.com/archives/34017