የዘፋኞች “እንጀራ” ከነእስክንድር ነጋ “እንጀራ“ በላይ ነው (በ”nahombetib”)

*ቦይኮቱ አስቴርና ጎሳዬን ሲነካ ደርሶ ድንገት የዘፋኝ መብት ተቆርቋሪ ለሆናችሁ

*ዘፋኞች የገዢው ስርዓት ድግሶችን ቢያደምቁ በንዴት “እቀባ  አታድርጉባቸው:: እንጀራቸው ሆኖ እንጂ ሕዝቡን ይወዱታል:: የት ሄደው ይዝፈኑ?” ለምትሉ

*ተራ ሕዝብንና ታዋቂ ዘፋኝን ለምታነጻጽሩ

*በሕዝብ ላይ በሚያሳድሩት የስነልቡና ተጽእኖ ለጨቋኙ ስርዓት የፕሮፖጋንዳ ሽያጭ የሚሰጡት የበላይነት ላልገባችሁ

*ከኮንሰርት በሚገኙ ገቢዎች ህወሓት እንዴት የገንዘብ ጡንቻውን እንደሚያፈረጥም ያልተረዳችሁ ወይም ግድ ያልሰጣችሁ

*አርቲስቶች ፈጽሞ አትዝፈኑ እንደተባሉና የአድማ ጥሪው የዘፋኝ ዳቦን ለማጥፋት የሚደረግ ለማስመሰል የምትሞክሩ

*ዘፋኞቹ ከህወሓት ኢህአዴግ ድግስ ውጪ በሌላ መንገድ ፈጽሞ ገቢ ማግኘት የማይችሉ ዓይነት አድርጋችሁ ለመሳል  ለምትታትሩ

* “የቦይኮት ስትራቴጂ ድክመት አለው፥ እንዴት፥ በምን መልኩ እንዲሻሻል መረዳት እችላለሁ” ከማለት ይልቅ የግል  ሕይወታቸው ሳያሳሳቸው ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ለማድረግ የሚጥሩ ወጣቶች ላይ ድንጋይ መወርወርን ለተካናችሁበት የተቃዋሚ ተቃዋሚዎች

*ዘፋኞች የፈለግሁበት አዘፍናለሁ ማለት መብታቸው እንደሆነ ሁሉ አክቲቪስቱ boycott፥ ዳያስፖራው ግንዛቤን እምቢኝ ማለት መብታቸው እንደሆነ ለጠፋችሁ

*Boycott ሰላማዊ የእቀባ ጥሪ ወይም ልመና እንደሆነ መረዳት ተስኗችሁ ቦይኮትን ከወያኔ ጥይት በላይ ለምታወግዙ

#የናንተን ምጡቅ አተረጓጎም ተጠቅመን ቦይኮትን እንደሚከተለው እናወግዛለን

1.ፌደራል ፖሊሶች ወይም አጋዚዎች ቢያስሩ ቢደበድቡ አልፎ አልፎ ቢገድሉ አትፍረዱባቸው:: እንጀራቸው ሆኖ እንጂ ጨካኝ ሆነው ተፈጥረው አይደለም:: ልጆቻቸውን ሌሎች ቤተሰቦቻቸውን በምን ያኑሩ? በዚያ ላይ ሁሉንም የሚያደርጉት ታዘው እንጂ ፈልገው አይደለም:: እነሱም እንደኛ የሕዝቡ አካል ስለሆኑ እባካችሁ አትጥሏቸው:: ብዙዎቹ ካሰሩ ከገደሉ በኋላ በጸጸት ፊታቸውን ማንም እንዳያያቸው በካኪ ዩኒፎርማቸው ሸፍነው ስቅስቅ ብለው ያለቅሳሉ።

2.ታዋቂ ሰዎችና ባለሃብቶች ….ኃይሌ፥ ቀነኒሳ… ከኢህአዴግ ጋር ቢሰሩ ቢተባበሩ አትርገሟቸው:: ይህን ባያደርጉ ሀበታቸውን ንግዳቸውን ሊያጡ ይችላሉ:: ቤተሰብ አላቸው… እንጀራቸውን ማጣት የለባቸውም:: እውነቱ እኮ ያለው ልባቸው ውስጥ ነው ሕዝቡን ይወዱታል

3.ብዙኅኑ ትግሬ ህወሓት በምንም መልኩ በመንግስትነት እንዲቀጥል ቢፈልጉ አታውግዟቸው:: ወደው እኮ አይደለም:: ይህን ባያደርጉ በዘዴ የማህበረሰብ መገለል ይደረግባቸዋል::

4.ህገወጥ ቤቶችን የሚያፈርሱ አፍራሽ ግብረኃይሎች የሕዝቡን ቤት በላዩ ላይ የሚንዱት መንግስት አዟቸው እንጂ ወደው-ፈቅደው አይደለም:: የእንጀራ ነገር ሆኖባቸው ነው::ካፈረሱ በኋላ ተጸጽተው ቤተስኪያን ሄደው ንስሐ ይገባሉ::

  1. አሁን ማን ይሙት ይሄ ሁሉ የቀበሌና ወረዳ ሹመኛ በመንግሥት ባይታዘዝ በገዛ ፈቃዱ የገዛ ወገኑ ላይ ይጨክናል? የእንጀራ ጉዳይ ባይሆን ሲያልፍም አይነካካው!

በመጨረሻም:-

ሕዝቡ ለወያኔ ቢገዛ ወዶ አይደለም ምን ያድርግ? ደኸነት ክፉ ደዌ የማያሳየው አበሳ የለም:: ፀጥ-ለጥ ብሎ ቢገዛ የደኸ ነፍሱን ለማዳን ከዚያም የዕለት እንጀራውን ለማግኘት ብሎ ነው::

እና ከላይ በተዘረዘሩት አተረጓጎሞች መሰረት የለውጥ እንቅስቃሴን ለፓለተከኛ ትተነዋል:: ግዴታው የነሱ ነው:: እነ እስክንድር፥ ተመስገን፥ ውብሸት፥ ዳርሴማ ሶሪ፥ ኤሊያስ ገብሩ… እነ ኮሎኔል ደመቀ፥ በቀለ ገርባ፥ ዶክተር መረራ፥ እማዋይሽ፥ ንግስት ይርጋ… ቤተሰብና እንጀራ የላቸውም::

===============================

መደምደሚያ:-

ቁምነገሩ ዘፋኞችን ከልቡ የሚወዳቸው “እባካችሁ አሳዳጄ ፥አሳሪዬ፥ ገዳዬ ድግስ ላይ አትገኙ:: ከሄዳችሁ፥ ዝግጅታችሁ ላይ አልገኝም፥ አድማለሁ::” የሚለው ነው:: ምክንያቱም የሚለምናቸው የተጽእኗቸውን ልክ ስለሚያውቅና ስለሚወዳቸው ነው::

Source Article from http://amharic.abbaymedia.com/archives/32347