የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ክስ ተመሰረተባቸው፤በ13 ሰዎች ሞት፣ለ109 ሰዎች የአካል ጉዳትና ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ውድመት ተጠያቂ ናቸው ተብለዋል

(በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)

ከነሐሴ ወር 2008 ዓ.ም ጀምሮ በባህር ዳር ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ክስ ተመሰረተባቸው፡፡

የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ በተከሳሾች ላይ ያቀረበው ክስ ተከሳሾቹ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆን ሲንቀሳቀሱ ቆይተው ነሀሴ 01 ቀን 2008 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ከባሀር ዳር ከተማ አስተዳደር ፈቃድ በመውሰድ ይህንን ሽፋን በማድረግ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ በመንቀሳቀስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌድሪ የወንጀል ሀግ አንቀፅ 32/1/ሀ፣35፣38፣27/1 እና 238/2 ን በመተላለፍ ለ13 ሰዎች ሞት፣ለ109 ሰዎች የአካል ጉዳትና ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እንዲወድም አድርገዋል የሚል ነው፡፡

ክስ የተመሰረተባቸው አመራሮች
1.ማሩ ዳኘው
2.መልካሙ ታደለ
3.እጅጉ አስማረ
4.ሲሳይ ተከለ
5.ወርቁ ጥላሁን
6.ታከለ ተመስገን
7.እንዳልካቸው ጥላሁን
8.ሃ/አ አስራት
9.ነገሰ ተፋረደኝ ሲሆኑ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ተራቁጥር የተጠቀሱት ተከሳሾች በእስሰር ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሀሴ 03 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ሀምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ ክስ ሳይመሰረትባቸው ቆይተዋል፡፡ ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ለሀምሌ 19 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

Source Article from http://amharic.abbaymedia.com/archives/32343