ወሎ ተርሻሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል- የህልም ዓለም !

ወሎ ተርሻሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታል- የህልም ዓለም ! Muluken Tesfaw

የወሎ ተርሻሪ ኬርና ማስተማሪያ ሆስፒታልን በተመለከተ በስዊድን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሠራተኛ የነበረ ደረጀ ገበሬ የሚባል የስቶክሆልም ነዋሪ ይህን ደብዳቤ ላከልኝ፡፡

በደብዳቤው እንደምትመለከቱት በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በሁሉም አገር ለሚሸጡ የድጋፍ ኩፐኖች መላካቸውን ሲሆን መንግሥትም ለዚህ ሥራ ዕውቅና ሰጥቶት ነበር፡፡ ሆኖም በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ በፓርላማ ለቀረበው ጥያቄ ‹‹በሕዝብ የሚገነባ ሆስፒታል አናውቅም፣ አንድ ሆስፒታል በወሎ ዩንቨርሲቲ ይገነባል›› የሚል መልስ ሲሰጥ ምን እንለዋለን? የተሠበሰበው ገንዘብ የት ደረሰ? ሁላችንም የተሻለ የጤና አገልግሎት እናገኛለን በሚል የለገስነው ገንዘብ የት ደረሰ? የሚሉ ጥያቄዎችን ማን ነው የሚመልሳቸው?


ጠቅለል ስናደርገው ወያኔ የዐማራን ሕዝብ የማያገኛቸውን የህልም ልማቶች በዲዛይን በማሳየት ገንዘብ ከመዝረፍ የዘለለ ምንም ሥራ እንደማይሠራ ማሳያ ነው፡፡ እንዲሁ መክነው ከቀሩት ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል የኮምቦልቻ ብረታብረት ኢንዱስትሪና የደብረ ማርቆሱ የመኪና ፕላንት ዋናዎቹ ናቸው፡፡