በኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ የሚገኘው ሀገሬ ዘይት ፋብሪካ ተቃጠለ

አባይ ሚዲያ ዜና

አሰግድ ታመነ

ዛሬ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ገደማ መንስዔው አልታወቀም በተባለ እሣት የተቃጠለው ዘይት ፋብሪካ 5 ሚሊዮን ብር የተገመተ ንብረት ወድሞበታል ተብላል፡፡

የእሣትና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን 35 የአደጋ ተከላካይ ሠራተኞች 5 ከባድ መኪኖችን በመጠቀም 53 ሺ ሊትር ውሃና 5 ሺ ሊትር ኬሚካል ፎም በእሣቱ ላይ አርከፍክፈዋል፡፡

ከሌሊቱ 10 ሰዓት ከ25 እስከ 11 ሰዓት ከ25 ገደማ ከነደደው እሣት 35 ሚሊዮን ብር የተገመተ ንብረት ማዳን መቻሉን ከባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ከአቶ ንጋቱ ማሞ ሰምተናል፡፡

ሀገሬ ዘይት ፋብሪካ የዛሬ አመትም እሣት አደጋ አጋጥሞት ብዙ ንብረት ያጣ ነው ተብሏል፡፡

በእሣት አደጋው በሰው ህይወትና አካል ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል፡፡

 

Source Article from http://amharic.abbaymedia.com/archives/29834