ደብረ ዘይት (ፍካሬ ኢየሱስ) በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ሊቃውንት አበው ዓለምን ሰውነታቸውን አካባቢያቸውን የተረጎሙበት፤ ዘመን የማይሽረው እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚዘልቅ ስለሆነና ያሁኗን ኢትዮጵያ የሚገልጽ ስለሆነ አቅርበንላችኋል።  ትምህርቱ በዳዊት መጽሐፍ ይጀምርና በማቴዎስ ምዕራፍ 24 ላይ ያተኩራል። ጥንታውያን አባቶቻችንና እናቶቻችን ፍካሬ ኢየሱስ ብለው ባጭር ቅጽ አዘጋጅተው ባንገታቸው ያደርጉታል። መጽሐፏ የያዘችው የነብያት፤ የክርስቶስ፤ የሐዋርያት፤ የቅዱሳን፤  ጻድቃን፤ የሰማዕታትና ያርበኞች መፈክር ነው።  ከለበስነው ሰውነታችን  ጀምሮ መፍረስ የሚጠብቀው ነው። እናቶቻችን አባቶቻችን ባንገታቸው አድርገውት ኖረዋል። የመውደቅንና የመነሳትን የምፍረስንና የመሰራትን መንፈስ የያዘች ናት።

ይልቁንም ዛሬ ኢትዮጵያን በመምራት ላይ ያለው ቡድን በተለምዶ አርበኛ የሚባለውን ቃል፤ እንደ ስድብ፣እንደ ውርደትና እንደ ጠላት አድርጎ  ለአንድ የህብረተሰብ ክፍል ብቻ በመስጠት አንገት ማስደፊያና ማሸማቀቂያ አድርጎ  እየተጠቀመበት ነው። ይህ ትምህርት አርበኛ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ጥልቅ ትርጉሙና እንዴት እንደተከሰተ የተገለጸበት ነው።

አርባ (40) የሰው ዘመን ወይም እድሜ ማዕከል ነው። “እመሰ በዝሀ  ሰማንያ ዓም ወፈድፋዶንሰ እም እላ ጻማ ወሕማም” ሰው በለበስነው ሥጋ በዚህ ዓለም እንደልቡ ተንቀሳቅሶ  የሚፈልገውን ሊያደርግ ቢችል በሰማኒያ አመት ውስጥ ነው። ከዚያ ካለፈ ወገቡ ይያዛል ቋንጃው ይቆረፍዳል፤ከራሱ ሰውነት ጋራ ጦርነት ውስጥ ነው የሚገባው።40ኛ ቁልቁለት ወርዶ አቀበት ወጥቶ አገሪቱን ከወራሪ ተከላክሎ፤ አርሶ  ቆፍሮ  አምርቶ ከወፍ ከአዕላፉ፤ ካላፊ ከአግዳሚ  የተረፈውን ባርክልኝ ብሎ ኢትዮጵያን የሚመግብ  አፍላ ማእከላዊ እድሜ ክፍል ነው። 40ኛ እድሜ በነብያት፤ በክርስቶስ፤ በሐዋርያት፤ በቅዱሳን፤  በጻድቃን፤ በሰማዕታትና ለአገር ለወገን ቤዛነት የተሰለፉ  መፈክር የሚያሰሙበት፤ ያሰሙትን መፈክር በተግባር የሚተረጉሙበት እድሜ ነው።  “በ40 ዕድሜ ክልል ያሉ ኢትዮጵያውያን ጎልማሶች፤  40ኞች እናታቸው ኢትዮጵያ  በመከራዋና በደስታዋ ከያሉበት መንደራቸው የምታድናቸው ዜጎች ናቸው” ይላሉ ሊቃውንት አበው። ቪዲዎውን ይመልክቱ፡

 

 

Source Article from http://www.mereja.com/amharic/531003