ጎንደር ለሁለተኛ ቀን ዛሬ በደረሰው የፈንጅ አደጋ ሰው ተጎዳ


10-1-2017

ከሙሉነህ ዮሃንስ

አሁን ከመሸ 2:00 ሰዓት አካባቢ ቀበሌ 18 ኢንታሳል ሆቴል ቦንብ ፍንድታ ነበር የተጎዳ ሰውም አለ ምን ያህል እንድሆነ መረጃውን እየተከታተልን ነው። እስካሁን ባለው ግን አንድ ሰው ሞቶ አንድ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል ተብሏል። ወያኔ የሚታወቅና እኩይ ባህሪው ፈንጅ እራሱ አፈንድቶ ህዝብ ለማንገላታት እንዲመቸው በተቃዋሚ ያሳብባል።
ይህ ብዙ ወያኔ የሚገባበት ሆቴል ነው የሚል መረጃ አለ። በተጨማሪ ይህ ሆቴል ዳሸን ቢራ በጣም የሚሸጥበት ቤት መሆኑ ተነግሯል። ዳሽን ብዙ ድርጅት መሸጥ አቁሞ ይህ ሆቴል ግን አፈንጋጭ ነው ተብሎለታል።ወያኔ በዚህ ሰበብ ብዙ ወጣት እየያዘ እየደበደበና እያሰረ ስለሆነ ጥንቃቄ ይደረግ።