TPLF እና ISIS አንድነት እና ልዪነታቸው – ሳሙኤል አሊ ከ-ኖርዌይ

tplf-addis-620x310

Isis ማለት በድብቅ ከሃያላን እና ሃብታም አገሮች ድጋፍ የሚደረግለት ሆኖ ሳለ በነዚህም አካላት አሸባሪ ተብሎ የሚከሰስ ድርጅት ነው። ISIS አላማው መቶ በመቶ ሰይጣኒዝም ሆኖ የሚፈጽማቸው ወንጀሎች በሙሉ ዘግናኝና የአለም ሚዲያወች በስፋት የሚያነጋግር ነው።

ወያኔ በግልጽ ከሃያላንና ከሃብታም አገሮች ድጋፍ የሚደረግለት ሆኖ ሳለ በነዚህም ድጋፍ ሰጪ አካል አሸባሪ ተብሎ ያልተከሰሰ ድርጅት ነው። ወያኔ አላማው መቶ በመቶ ኢትዮጵያን የማጥፋት ስራውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ያለማቃረጥ ለ25 አመት በትጋት እየሰራ ሲሆን የሚፈጽማቸው ዘግናኝ ወንጀሎች በሚዲያ ላይ ጎልተው የማይታዩ ናቸው።

ISIS አለም አቀፍ አሸባሪ ሆኖ የሚንቀሳቀስ አካል ነው። የራሱ የሆነም ክልሎችን ከልሎ እስላማዊ መሬት ብሎ በመጥራት በከለላቸው መሬት ላይ ያሉትን ንጹሃን እሱ ባስቀመጠው ህግ የማይሄዱትን በሙሉ የማጥፋት ስራ የሚሰራ አሸባሪ ቡድን ነው ።

ወያኔ አገር አቀፍ አሸባሪ ሆኖ እራሱን ግን እንደመንግስት ሰይሞ የሚንቀሳሰስ አካል ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔዝምን በማስፋፋት በአገሪቱ ላይ ያሉት ዜጎች እሱ ባስቀመጠው ህገ አራዊት የማይሄዱትን በሙሉ የሚያጠፋ አገር በቀል አሸባሪ ሆኖ የአገሩን ሰው የሚያሸብር ነው ።

ISIS ህጻናትንና ሴቶችን አይገልም ህጻናቱን ግን የሱን የጥፋት ትምርት በማስተማር ተጣመው እንዲያደርጉ አድርገው የነሱን አላማ አስፈጻሚ አድርገው የመቅረጽ ስራ ይሰራባቸዋል። ሴቶችን ደግሞ ተይዘው በአንድ አካባቢ ያስቀምጡቸውና የዝሙት ባርያቸው ያደርጉአቸዋል። ማንኛውም የisis አባል የሆነ ወንድ ታግተው ከተያዙት ሴቶች መሃል የፈለገውን ያህል ይመርጥና ዝሙት ሊፈጽምባቸው ይችላል። ይሄ ታድያ የISIS ህግ ነው።

ወያኔ ህጻናትን የራሱን የጥፋት ፖለቲካ በማስተማር ለጥፋት ስራው ቀረጻ የሚያዘጋጀቸው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህጻናትን የመለመለ አሸባር ነው። እነዚህ የወያኔን ሃሳብ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያድጉ የሚደረጉትን ህጻናት ከሌላው ሰው ጋር የማይገኛኙ ከህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ የማይፈቀድላቸው ተገለው የሚኖሩ ናቸው እነኚህ ህጻናት የሚማሩት ትምህርት ስለ ትግራይ ህዝብ ታላቅነት፣በታሪክ ሌላው ህዝብ የትግራይን ህዝብ ሲያጠፍ የኖረ፣ የትግራይ ህዝብ እንዲኖር የማይፈልግ ነው የሚል ነው። ይህ ኢሰባዊ የሆነ የወያኔ ስራ ነው ።

ISIS የጥፋት ስራው ከግዜ ወደ ግዜ እየሰፋ እና እየከፋ በመምጣቱ አገሮችን እስከማጥፋት ውስጡ ያሉትን ህዝቦችንም እስከመበተን የደረሰ አሰቃቂ ጥፋት እያደረሰ ነው። ለዚህም ኢራቅና ሶርያ ተጠቃሽ ናቸው። በ ISIS የግፍ እንቅስቃሴ ሚሊዮኖች ሃብት ንብረታቸውን አጥተዋል ሚሊዮኖችን የሰቀቀን ሂወት እንዲኖሩ አድርጋል ።

ወያኔ የጥፋት ስራው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሰፋ እና እያከፍ ከመምጣቱ በፊት በድብቅ ይሰራቸው የነበሩትን ወንጀሎች አሁን በግልጽ እየፈጸመ ይገኛል። ገና ከጅምሩ ከደደቢት በርሃ ሲነሱ ቀርጸውት የመጡትን ህግ ለ25 በባርነት እየገዙት ባሉት ኢትዮጵያዊ ላይ እየተገበሩት ይገኛል። ኢትዮጵያ የምትባለዋን የጀግኖች አገር ለማጥፋት ቆርጠው በመነሳት በሁሉም ክልሎች ሲላቸው በጅምላ ሲላቸው በተናጥል በመግደል እና ሃብት ንብረቱን በመንጠቅ ፤ ሚሊዮኖችን አስርበዋል፤ ሚሊዮኖችን አገር አስጥለው አሰድደዋል ፤ሚሊዮኖች የሰቆቃ ህይወት እንዲኖሩ እያደረጉ ነው።

ISIS ጋዜጠኞችን ታዋቂ ሰወችን የሚቃወሙአቸውን የፖለቲካ ሰወችን በዘግናኝ ሁኔታ በመግደል የአለምን ትኩረት ለመሳብ ይሞክራሉ።

ወያኔ ጋዜጠኞችን በማሰር ታዋቂ ሰወችን ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ በፖለቲካ ከሱ አካሄድ የተለዩትን በመግደል በማሰር አፈናውን በአገር ውስጥ በማከናወን ለአለም ሚዲያ ግን ምንም ችግር እንደሌለ አገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ ልማት ላይ እንዳለች የውሸት በሬ ወለደ የሆነውን ፕሮፖጋንዳ ይነዛሉ።

ISIS በዚች አለም ውስጥ ሊኖር የማይገባው ተቋም ሆኖ ሳለ ነገር ግን ውስብስብ በሆነ ሁኔታ እንዲጠፋ የማይፈልጉ አካሎች መኖራቸው ቢያሳዝንም ቅሉ ሩስያ አሁን እየወሰደች ያለችው እርምጃ አስደሳች እና ISIS በቅርብ ጊዚያት ውስጥ አሸመድምዶ ከምድረ ገጽ ሊያጠፋው እንደሚችል የብዙዎች ግምት ነው።

ወያኔም በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሊኖር የማይገባው ተቋም መሆኑን አለም ሁሉ ቢያውቁም ነገር ግን ምክንያቱን ለመግለጽ በሚያስቸግር መልኩ እንዲኖር የሚፈልጉም አካሎች መኖራቸው ቢያሳዝንም ቅሉ እኛ ሁላችን በአንድነት ወያኔን በትጥቅ ትግል እንጥላለን ብለው በርሃ ከገቡት እና በቅርቡም የአንድነት ጥምረትን ፈጥረው እየተንቀሳሰሱ ከሚገኙት ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ሆነ በየትኛውም መንገድ ወያኔን ከኢትዮጵያ ምድር ጠራርገን ለማስወጣት አገር በማዳኑ ስራ ሁሉም ሕብረተሰብ ቆርጦን መነሳት ያለብን ወቅት ላይ እንገኛለን።

ወያኔን ከቅድስቲቷ አገር ከኢትዮጵያ ISIS ከአለማችን ላይ የማጥፋቱ ስራ ተጠናክሮ በመቀጠል የተረጋጋች አለም እና በፍቅር የታነጸች ኢትዮጵያን ለመገንባት ሁሉም አስተዋጽኦ ያድርግ።

እግዛአቤሔር ኢትዮጵያችንን ይጠብቅልን

ሳሙኤል አሊ ከ- ኖርዌይ

Email [email protected]

07.10.2015

Source:: Zehabesha